የወላይታ ዞን ዳግም ህዝበ ውሳኔ በትናንትናው እለት ተጠናቆ በየምርጫ ጣቢያው ውጤት እየተለጠፈ መሆኑ ተገለጸ።
ዳግም ህዝበ ውሳኔው ምርጫ የጎላ የህግ ጥሰት ሳያስተናግድ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል ።
በአሁኑ ወቅት በየምርጫ ጣቢያው የተለጠፈው ውጤት ወደ ምርጫ ጣብያ ማዕከላት ተልኮ የማዳመር ስራ እየተሰራ መሆኑም ነው የተገለፀው፡፡
በዞኑ 12 የምርጫ ጣቢያ ማዕከላት ማስተባበርያና 1 ሺሕ 812 የምርጫ ጣብያዎች እንዳሉ ይታወቃል።
ዋልታ
