ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ስማርት የመማሪያ ክፍል አስጀመረ
ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ስማርት የመማሪያ ክፍል ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አራት ኪሎ ግቢ በመገንባት ዛሬ ሥራ ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር)፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ጣሰው ወልደሃና(ፕ/ር)፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ የስማርት የመማሪያ ክፍሉ…
