Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

በትግራይ ክልል ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቀሉ

በትግራይ ክልል የነበሩ ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ መቀላቀላቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ም/ርዕሰ መስተዳድርና ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ፡፡

ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ በክብር ሽኝት ተደርጎላቸዋል ብለዋል፡፡

ይህም የትግራይ ሕዝብ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያለውን ዝግጁነት ያሳያል ነው ያሉት፡፡

ወደ ሕብረተሰቡ የተቀላቀሉ የቀድሞ ታጣቂዎችን ለማቋቋም ቀጣይነት ያላቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች እንደሚሠሩ አንስተዋል፡፡

ሽኝት የተደረገላቸው የቀድሞ ታጣቂዎችም በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች አቀባበል እየተደረገላቸው ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *