Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ የተሰጠ መግለጫ

በአማራ ክልል እየተከናወነ ያለው የህግ ማስከበር ተግባር በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ክልሉን ወደ ሰለማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ እዝ አስታወቀ፡፡በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መጠየቁ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም የሚኒስትሮች ምክር ቤት…

አማርኛ ዜና
0

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወሰነ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ በሙሉ ድምጽ ወሰነ። ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 ላይ ነው፡፡ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚታየውን በትጥቅ የተደገፈ ህገወጥ እንቅስቃሴ በመደበኛ የህግ ማስክበር ስርዓት ለመቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ደረጃ…

አማርኛ ዜና
0

በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ሥርዓት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ።

በአማራ ክልል የተከሰተው የሰላም መደፍረስ በክልሉ ከፍተኛ ሰብአዊ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እያደረሰ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ለማዋል እስካሁን በክልሉና በፌደራል የፀጥታ ሃይሎች በኩል በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል። ሆኖም በክልሉ ያለው የፀጥታ መደፍረስና ጥቃት በንፁሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት በአስቸኳይ ለማስቆም የፌደራል መንግስት ከመደበኛው የህግ ማስከበር ስርአት ባሻገር በኢፌዴሪ…

አማርኛ ዜና
0

የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሀገር እና የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት 15ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ነው። በጉባኤው ላይ የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የሀይማኖት ተቋሙ የሰላም እና እሴት ግንባታ ላይ ለመስራት የድርሻውን እየተወጣ ነው ተብሏል። በሀገሪቷ ህዝቦች እና የእምነት ተቋማት ላይ ያለውን ለዘመናት የቆየ የመከባበር ባህል በማጠናከር ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ሀይማኖታዊ እሴትን መሰረት አድርጎ እየሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው።…

አማርኛ ዜና
0

ዩክሬን በምዕራባውያን የጦር ታክቲኮች ተስፋ ቆርጣለች – ኒዮርክ ታይምስ

ዩክሬን የሩሲያን ጦር ለመመከት ምዕራባውያን ባሳዩዋቸው የጦር ታክቲኮች ተስፋ ቆርጣለች ሲል የአሜሪካው ኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ኒዮርክ ታይምስ እንደዘገበው÷ በኔቶ የተሳሳተ የጦር እቅድ ምክንያት ዩክሬን ከባድ ወታደራዊ ኪሳራ አጋጥሟታል፣ ወታደሮቿንም እሳት ላይ ጥዳለች ብሏል፡፡ በመሆኑም የዩክሬን ጦር ምዕራባውያን የቀየሱለትን የጦር ታክቲክ ወደ ጎን በመተው ከሩሲያ ሀይሎች ጋር በረጅም ርቀት የመዋጋት ስልትን ለመከተል መወሰኑ ነው የተገለፀው፡፡…

አማርኛ ዜና
0

“በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች አሳሳቢ እየሆኑ መጥተዋል” – ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በማህብራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሀፍ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢውች የሚታዩ የጸጥታ ችግሮች አሳሳቢ እየሆኑ መጥተዋል ብለዋል። በመሰረቱ ብዙ ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች ይኖራሉ ያሉት ደመቀ መኮንን እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ግን ጠቃሚው መንገድ ሰላማዊና የውይይት አግባብ ነው ብለዋል። ከዚህ ውጭ ያለው አካሄድ ‘ሰላም ከሌለህ ሁሉን ታጣለህ’ የሚባለውን…

አማርኛ ዜና
0

መሬት በሊዝ ወስደው ያላለሙ 68 ባለሃብቶች ውል ተቋረጠ

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 90 ሄክታር መሬት በሊዝ ወስደው ያላለሙ 68 አልሚዎችን ውል ማቋረጡን እና 1 ሺ 283 አልሚዎች ግንባታ እንዲጀምሩ መወሰኑን አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም አስመልክቶ በተካሄደው ግምገማ ላይ እንደተናገሩት፤ አንዳንድ አልሚዎች መሬት ከተቀበሉ በኋለ በወቅቱ ግንባታ ሳይጀምሩ ለረጅም ዓመታት አጥረው ያስቀምጣሉ። ነገር ግን የሊዝ ሕጉ…

አማርኛ ዜና
0

‹‹ኢትዮጵያ ዋነኛ የጀርመን የልማት አጋር ነች›› በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ዋነኛዋ የጀርመን አጋር ናት ሲሉ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ጀርመን በተለያዩ ዘርፎች አጋርነት ከፈጠረችባቸው 12 የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ዋነኛዋ ናት። ኢትዮጵያና ጀርመን በሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆን በባለብዙ ወገን ግንኙነትም ላይ በንቃት ተሳትፏቸውን እያሳደጉ ይገኛል። እንደ አምባሳደር ስቴፈን…

አማርኛ ዜና
0

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መቀበል መጀመሩን አስታወቀ

መቐለ ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት በ2013 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎችና የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አሰታወቀ። ዩኒቨርስቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው ተመራቂ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል። በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለ2 ዓመታት ሲካሄድ የቆየውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አገልግሎት መስጠት ማቋረጣቸው አይዘነጋም። ዩኒቨርሲቲው ከፌዴራል መንግሥት በተለቀቀለት በጀት ተማሪዎችን መቀበል የሚያስችለውን ዕድሳት እና…

አማርኛ ዜና
0

“የተቋሙን ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ የአየር ኃይል ጥበቃ ክፍለ ጦር ውጤታማ ተግባር እያከናወነ ነው” ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

የተቋሙን ደህንነት በማረጋገጡ ረገድ የአየር ሃይል ጥበቃ ክፍለ ጦር ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ ነው ሲሉ የአየር ሃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ። አዛዥ ይህን የተናገሩት በጥበቃ ክፍለ ጦር የሥራ ቦታ የተሰሩትን ቢሮዎች የመዝናኛ ቦታዎችን እና የልማት ስራዎችን ተዘዋዉረው ከጎበኙ በኋላ ነው። የአየር ኃይል ጥበቃ ክፍለ ጦር የተቋሙን ደህንነት እና ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ ከዚህ በፊት እንደችግር…

አማርኛ ዜና
0

የአማራ ክልል ወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ የሚመክር ውይይት በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው

የአማራ ክልል ወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ የሚመክርና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ መድረኩን አስመልክቶ እንደገለፁት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የሰላም ችግር በጋራ ተወያይቶ መፍትሄ ለማምጣት ያለመ ውይይት ነው። በአሁኑ ወቅት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር እና ህብትና ንብረት የማጥፋት…

አማርኛ ዜና
0

በ”ፋኖ” ስም እየተንቀሳቀሱ የሃገር ሰላም ለማወክ በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል- የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት

አሁናዊ የመከላከያ ሰራዊቱን ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የሰራዊቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፣ መግለጫው በተለያዩ አካላት በሰራዊቱ ላይ እየተናፈሱ ያሉ ብዥታዎችን ለማጥራት የተሰጠ ነው ብለዋል። ሰራዊቱ ካለፉት ዓመታት በነበረበት ቁመና ላይ እንዳለ የሚያስቡ አካላት ካሉ የቆሙት እነርሱ እንጂ ሰራዊቱ ተራማጅ ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፣…

አማርኛ ዜና
0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት በአጠቃላይ የኢትዮጵያን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ላይ ገለጻ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷”የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የትብብር አድማስ በማስፋት ለኢኮኖሚ እድገታችን በኮንሴሽናል ፋይናንስ፣ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በኩል ጠንካራ የኢንቨስትመንት…

አማርኛ ዜና
0

ሩሲያ የዩክሬንን እህል የመላክ ስምምነት እንድታከብር የግብጹ መሪ አሳሰቡ

የሩሲያው ፕሬዛዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባስተናገዱት የሩሲያ አፍሪካ ስብሰባ ላይ የግብጹ ፕሬዛዳንት ጠንከር ያለ ሃሳብ አንስተዋል። ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ዩክሬን እህል ወደ ውጭ እንድትልክ የሚያስችለው ስምምነት በፍጥነት እንዲታደስ የሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲንን በብርቱ አሳስበዋል። ስምምነቱ “ወሳኝ” ነው ያሉት አብድል ፈታህ አል ሲሲ፣ ችግሩ በፍጥነት ተቀርፎ ድሃ አፍሪካውያን መፍትሄ ሊያገኙ ይገባል ብለዋል። ሩሲያ ከስምምነቱ የወጣችው ባለፈው ሳምንት…

አማርኛ ዜና
0

ሩሲያ በዩክሬኗ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤት እና የደኅንነት ሕንጻን በሚሳኤል ደበደበች

በምስራቃዊ ዩክሬን በምትገኘው ዲኒፕሮ ከተማ ትናንት ሌሊት [አርብ] ሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት ፈጽማለች። በጥቃቱ የጋራ መኖሪያ ቤት እና አንድ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ሕንጻ ኢላማ ተደርገዋል። የከተማዋ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት በጥቃቱ ቢያንስ 9 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ሁለቱ ሕጻናት መሆናቸው ታውቋል። የቢቢሲ የዘገባ ቡድን በስፍራው ተገኝቶ እንዳረጋገጠው የጋራ መኖሪያ ቤት ጣሪያ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተደርምሷል። ንብረትነቱ የዩክሬን የደኅንነት…

አማርኛ ዜና
0

ዩክሬን ከሩሲያ ትውፊቶች ራሷን ለማራቅ የገና በዓልን ዕለት ቀየረች

ዩክሬን የገና በዓል መላው ሩሲያን ጨምሮ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ከሚያከብሩበት ታህሳስ 29 ወደ ታህሳስ 16 ወይም ወደ ጎሮጎሳውያኑ ታህሳስ 25 እንዲዛወር ወሰነች። ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ “ ከሩስያ የተወረሰውን የገና በዓል አከባበር ትውፊት” ለማስወገድ ያለመ የፓርላማ ህግን ፈርመዋል። ዩክሬን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሩሲያ ጋር ያላትን ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ሌሎች ግንኙነቶችን በመቁረጥ ከምዕራቡ ዓለም ጋር አጋርነትን መርጣለች። በተለይም…

አማርኛ ዜና
0

በኦሮሚያ ክልል በ24 ቢሊየን ብር ወጪ 6 ሺህ 81 ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል

በ2015 በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል 6 ሺህ 81 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክተር ሃሰን እንድሪስ÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ በተለይም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እና አስፈላጊ የትምህርት ግብዓቶችን ለማሟላት በቅንጅት ተሰርቷል ነው ያሉት፡፡ በዚህ መሰረት…

አማርኛ ዜና
0

አሜሪካ በመፈንቅለ መንግሥት የተወገዱት የኒጀር መሪን እንደምትደግፍ ገለጸች

አሜሪካ በመፈንቅለ መንግሥት ለተወገዱት የኒጀር ፕሬዚዳንት መሃመድ ባዙም “ያላሰለሰ ድጋፍ” እንደምታደርግ ገለጸች። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት መሃመድ ባዙም በክቡር ዘብ መሪያቸው ጄነራል አብዱራህማኔ ቺያኒ ወይም በተለምዶ ኦማር ቺያኒ በተመራ መፈንቅለ መንግሥት ከስልጣናቸው ተነስተዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መሪውን መሃመድ ባዙምን በቁጥጥር ስር ላዋሏቸው ግለሰቦች ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። ለአገሪቱ የሚደረገው “በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር እርዳታ”ንም አደጋ ውስጥ እንደሚከተው…

አማርኛ ዜና
0

በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የመረጃ፣ የቢዝነስና የመሰረተ ልማት ትብብር የሚያጠናክር ስምምነት ተፈረመ

በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የመረጃ፣ የቢዝነስና የመሰረተ ልማት ትብብር የሚያጠናክሩ ስምምነቶች ተፈረሙ። ስምምነቶቹ በሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ በሚገኘው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን አባላት የተፈረሙ ናቸው ተብሏል። በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል አለም አቀፍ የመረጃ ደህንነትን በተመለከተ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ናቸው። ስምምነቱ በአለም አቀፍ…

አማርኛ ዜና
0

የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ

ባለፉት ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው 2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡ አገልግሎቱ በሂደቱ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡ የሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢና ሳውላ ካምፖስ ተገኝተው…

አማርኛ ዜና
0

ቀድመው ለሚዘሩ ሰብሎች ማዳበሪያ እንዲደርስ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ቀድመው ለሚዘሩ ሰብሎች የአፈር ማዳበሪያ እንዲደርስ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ። የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የማዳበሪያ አቅርቦትን ጨምሮ በወቅታዊ የግብርና ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በዚህ አመት ያጋጠመውን የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር እንዳይደገም ከወዲሁ የቀጣዩን ዓመት የማዳበሪያ ግዢ ለመፈጸም መታቀዱን ተናግረዋል። ከጫረታ የማዳበሪያ ግዥ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችንም በመጠቀም ችግሩን ለመፍታት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። የዚህ ዓመት የማዳበሪያ…

አማርኛ ዜና
0

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአፍሪካ እህል በነፃ ለማቅረብ ቃል ገቡ

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ምዕራባውያን የጥቁር ባሕር እህል ስምምነትን ላልተገባ ጥቅም በማዋል “እፍረት የለሽ” ድርጊት ፈጽመዋል በማለት ወቅሰዋል። ፕሬዚዳንቱ ለአፍሪካ ነፃ እህል ለማቅረብ ቃል የገቡ ሲሆን፣ በሀገራቸው እና በአህጉሪቱ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ እ.ኤ.አ. በ2022 ከደረሰበት የ18 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚያድግ ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል። በሴንት ፒተርስበርግ ከሚካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በፊት በሰጡት መግለጫ፣ አፍሪካ በቡድን 20…

አማርኛ ዜና
0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሀገራዊ ሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ በኮንስታንቲኖቭስኪ ቤተ መንግሥት በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በውይይታቸውም ሁለቱ መሪዎች በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ እና ታሪካዊ ግንኙነት በማጠናከር የንግድ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በግብርና እና በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ዙሪያ በትብብር ለመሥራት ያላቸውን…

አማርኛ ዜና
0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ገብተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልኡካን ቡድናቸው ቅዱስ ፒተርስበርግ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በክብር ዘብ ሰላምታ የታጀበ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በከተማው የሚገኘውን እና በሁለተኛው የአለም ጦርነት የተሰዉ የሩሲያ ሠማእታትን ለመዘከር የአበባ ጉንጉን የማኖር ስነ-ሥርአትም አከናውነዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተገነባውን ሙዚየምም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተዘዋውረው…

አማርኛ ዜና
0

በትግራይ ክልል ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ ተቀላቀሉ

በትግራይ ክልል የነበሩ ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ መቀላቀላቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ም/ርዕሰ መስተዳድርና ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ፡፡ ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ከ55 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ በክብር ሽኝት ተደርጎላቸዋል ብለዋል፡፡ ይህም የትግራይ ሕዝብ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያለውን ዝግጁነት ያሳያል ነው ያሉት፡፡…

አማርኛ ዜና
0

የኢትዮጵያ አጎዋ ዕድል ማንሰራራት እና የቀጠለው የቮን ባተን ሞንታግ ሙግት

የአሜሪካ መንግሥት ከትግራዩ ጦርነት ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያን ለአፍሪካ አገራት ከሚሰጠው የቀረጥ ነጻ ንግድ ዕድል (አጎዋ) መሰረዙን ያስታወቀው በጥቅምት 2013 ነበር፡፡ ኢትዮጵያን ከቀረጥ ነጻ እድሉ ያስወጣት ጦርነት በሠላም ስምምነት ከተቋጨ ከ10 ወራት ገደማ በኋላ ደግሞ የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ ዕግድ ይነሳ ወይስ ፀንቶ ይቆይ በሚለው ላይ የመጀመሪያውን ውይይት አድርጓል፡፡ በጉዳዩ ላይ የሚመክረው በአሜሪካ የአጎዋ ንዑስ ኮሚቴ ከባለድርሻ…

አማርኛ ዜና
0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር የተናጠል ውይይት እንደሚያደርጉ ተገለጸ

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሩሲያ-አፍሪካ ስብሰባ ላይ እንደሚሳተፉ እና ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የተናጠል ውይይት እንደሚያደርጉ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ረዳት አስታወቁ። በአፍሪካ አገራት እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር በሚል ከሐሙስ ሐምሌ 20/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈርቂም ወደ ሩሲያ ማቅናታቸው ተገልጿል። በሴንት ቢተርስበርግ ከሚካሄደው ስብሰባ ጋር በተያያዘ…

አማርኛ ዜና
0

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከጣሊያን አቻቸው ኤድሞንዶ ቺሬሊ ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከጣሊያን አቻቸው ኤድሞንዶ ቺሬሊ ጋር ተወያዩ። ውይይታቸውም በዋናነት የሁለቱ አገራት ግንኙነት በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በዚህም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር አገራቱ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከጣሊያን ጋር ያላትን ሁለንተናዊ የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደምትሻ አምባሳደር ብርቱካን ተናግረዋል። ጣሊያን ከኢትዮጵያ…

አማርኛ ዜና
0

“የሩሲያ – አፍሪካ አጋርነትና ግንኙነት ጠንካራ ጥልቅ እና ፅኑ በመተማመን እና በበጎ ፈቃደኝነት ላይ መመስረቱ መለያው ነው፡፡” የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

“የሩሲያ- አፍሪካ አጋርነትና ግንኙነት ጠንካራ ጥልቅ እና ፅኑ በመተማመን እና በበጎ ፈቃደኝነት ላይ መመስረቱ መለያው ነው፡፡” ሲሉ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገልጸዋል፡፡ በሩሲያዋ ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ሐምሌ 20 እና 21 ሁለተኛው የሩሲያ -አፍሪካ የኢኮኖሚና የሰብዓዊ ፎረም ይካሄዳል፡፡ፎረሙን አስመልተው የሩሲያው ፕሬዝንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላኩት ፅሁፍ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን የዳሰሱ ሲሆን በዋናነት አገሮች እና…

አማርኛ ዜና
0

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 16 ቢሊዮን ብር የነዳጅ ድጎማ ተደርጓል

በ2015 በጀት ዓመት መንግሥት ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች 16 ቢሊዮን ብር የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ከድጎማ ሥርዓቱ 180 ሺህ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የነዳጅ ውጤቶች ገበያ ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015 በጀት ዓመት መንግሥት ለ180 ሺህ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት…

አማርኛ ዜና
0

በጅማ ከተማ ሁለት ትላልቅ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው

በጅማ ከተማ ሁለት ትላልቅ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡ የጅማ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዋሴ ግርማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቶቹ የሚገነቡት ከተማዋን አቋርጦ በሚያልፈው አዌቱ ወንዝ ላይ ነው፡፡ አዌቱ ፔይስትሪ ፕሮጀክት ለሦስት ዓመት ያህል እየተገነባ ያለ ሲሆን ፕሮጀክቱ ብዙ ጥቅም እንደሚሰጥ ታስቦ የተጀመረ ነው፡፡ የአዌቱ ወንዝ ከዚህ ቀደም በኅብረተሰቡ…

አማርኛ ዜና
0

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በቡኖ በደሌ የሩዝ ኢንሼቲቭ ልማትን በይፋ አስጀመሩ

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በቡኖ በደሌ ዞን በበደሌ ወረዳ የሩዝ ኢንሼቲቭ ልማትን በይፋ አስጀመሩ። የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውጥ ማምረትና የሥራ እድል መፍጠር የመንግሥት ቁልፍ ተግባራት መሆኑን አቶ ሸመልስ ተናግረዋል። በዚህም የስንዴ ምርት ከውጭ ማስገባት ቀርቶ ወደ ውጭ መላክ እንደ ተጀመረ ሁሉ በሩዝ ምርትም ለመድገም መታቀዱን አንስተዋል። በዞኑ 114 ሺህ…

አማርኛ ዜና
0

ዕንባ ጠባቂ ተቋም ውሳኔውን ባልተገበሩ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ላይ ክስ መሥርቻለሁ አለ

ውሳኔውን ባልተገበሩ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ላይ ክስ መመሥረቱን፣ የኢትዮጵያ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡ ውሳኔውን ባልፈጸሙ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ላይ የተጠያቂነት ሥርዓትን በተመለከተ በ2015 በጀት ዓመት በ24 መዝገቦች ላይ የወንጀል ክስ መመሥረቱን፣ ከእነዚህ መካከል ዘጠኑ ክሶች ውሳኔ እንዳገኙና 15 መዝገቦች ደግሞ በክስ ሒደት ላይ መሆናቸውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ክስ የተመሠረተባቸው ተቋማት የባህር ዳር ከተማና የአሶሳ…

አማርኛ ዜና
0

ከፍርድ ውጪ ለዓመታት ታስረዋል የተባሉ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች እንዲለቀቁ ተጠየቀ

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዋች ካለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለዓመታት ታስረዋል የተባሉ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አመራሮች እንዲለቀቁ ጠየቀ። ሂዩማን ራይትስ ዋች ባወጣው መግለጫ ሰባቱ ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች በፖለቲካ ተሳትፏቸው ብቻ ለሦስት ዓመታት ያህል በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የኢትዮጵያ መንግሥት የፍትሕ ሥርዓቱን ማሻሻል እንዳለበት ማሳያ ነው ብሏል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ኦሮሚያ ፖሊስ አብዲ…

አማርኛ ዜና
0

ሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ የተባለውን አገልግሎት መስከረም ላይ በኢትዮጵያ እንደሚጀምር ገለጸ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፤ ኤም-ፔሳ የተሰኘው የሞባይል ገንዘብ መላላኪያ አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምር ገለጸ። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እናት ድርጅት የሆነው ቮዳኮም ግሩፕ ሊሚትድ የኤም-ፔሳ አገልግሎት መስከረም 2016 ዓ.ም. አጋማሽ እንደሚጀመር ገልጧል። ቮዳኮም ግሩፕ የ2023 አንደኛ ሩብ ዓመት በዳሰሰበት መግለጫው በሁለተኛው ሩብ ዓመት ኤም-ፔሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ይጀምራል። እአአ ጥቅምት 2022 ሥራ የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከ2.7 ሚሊዮን ባለይ ደንበኞች ማካበቱን መግለጫው…

አማርኛ ዜና
0

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ), ጋምቤላ በተመለከተ ያስወጣው መግለጫ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ የጋምቤላ ክልል አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩ የትጥቅ ግጭቶችን፣ የታጠቁ ቡድኖች ጥቃቶችንና አጠቃላይ የጸጥታ ችግሮችን እና በዚህ ሳቢያ የሚደርሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ተጎጂዎችን፤ የአካባቢዎቹን ነዋሪዎች እንዲሁም የክልሉን የጸጥታ እና የአስተዳደር ኃላፊዎችን በማነጋገር ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በላከልን መግለጫ አሳውቋል። በተለይ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በክልሉ…

አማርኛ ዜና
0

ከቡና የወጪ ንግድ ከአንድ ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል

በ2015 በጀት ዓመት ከቡና የወጪ ንግድ ከአንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳሕለማርያም ገብረመድህን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2015 በጀት ዓመት 360 ሺህ 144 ቶን ቡና በላይ በመላክ አንድ ነጥብ 8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 240 ሺህ…

አማርኛ ዜና
0

” እኛ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ እየጠበቅን ነው ” – ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ

የአማራ እና የትግራይ ክልሎች የሚዋሰኑባቸውን የወልቃይት፣ የጠለምትና የራያ አካባቢዎችን ” ይገባኛል ” ጥያቄን በተመለከተ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ እየተጠበቁ መሆናቸውን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል አሳውቀዋል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በአሁን ሰዓት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ  ምክትል አስተዳዳሪ እና የሰላምና የፀጥታ መምርያ ኃላፊ በመሆን እያገለገሉ ሲሆን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ…

አማርኛ ዜና
0

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረገው የአፍሪካ ኅብረት እውቅና ተሰጠ

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረገው የአፍሪካ ኅብረት እውቅና ተሰጠ፡፡ እውቅናውን የሰጠው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሆን በዚህም ለአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ደኅንነት ኮሚሽን እንዲሁም ቡድን የእውቅና መርኃ ግብር ተካሂዷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በቅርቡ አፍሪካ ኅብረት ላደረገው አስተዋጽኦ በአጠቃላይ እና ኢትዮጵያ የሰጠችውን እውቅና አስታውሰዋል። በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም…

አማርኛ ዜና
0

በማክሰኝት ከተማ ስድስት የመንግስት የፀጥታ ኋይሎች መገደላቸው ተረጋገጠ።

ከጎንደር ከተማ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ማክሰኝት ከተማ፤ ረቡዕ ሐምሌ 12/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በአገዛዙ ወታደሮች እና በፋኖ መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሦስት ፖሊስና ሦስት ሚሊሻ በድምሩ ስድስት የአገዛዙ የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም አንድ ነዋሪ መገደላቸውን መረጃ ቲቪ ከነዋሪዎች አረጋግጧል። የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል የተጠቆመ ሲሆን፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የጸጥታ አካላት፣…