Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

600 በሚሆኑ ከተሞች ህግ የማስከበር ስራ እየተሰራ ነው – የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ


በኦሮሚያ ክልል 600 በሚሆኑ ከተሞች ህግ የማስከበር ስራ እየተሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በወቅታዊ የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም የተወሰደው እርምጃ ያለ ፕላን የተሰሩና በህገ-ወጥ መንገድ የተገነቡ ግንባታዎችን ህግ ለማስከበር ማዕከል ተደርጎ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ማህበረሰቡ እምነትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን ተገንዝቦ ከፅንፈኞች ፕሮፖጋንዳ እንዲጠነቀቅ መልዕክት ተላልፏል።

ከዚህ በፊት ህገወጥ ቤቶቹ ሲገነቡ ህግ ያላስከበሩ አካላትንም በህግ የማስጠየቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በመግለጫው አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *