Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
ዜና ትግርኛ
0

371ሺህ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ዝግጅት እየተደረገ ነው


371ሺህ የሚደርሱ የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ ለመሥራት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ገለጸ፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በሰሜኑ ጦርነት እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች የፖለቲካ ዓላማቸውን በትጥቅ ለማስፈጸም ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና በአሁኑ ጊዜ ወደ ሰላማዊ ትግል ለመግባት የወሰኑ 371 ሺ የሚደርሱ የቀድሞ ተዋጊዎችን በአንድ ቦታ የማሰባሰብ እና መልሶ የማቋቋም ሥራዎችን ለመሥራት ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

ኮሚሽኑ እስከ አሁን ባሉት የተወሰኑ ወራቶች ተቋሙን ማቋቋም፣ በሰው ኃይል ማጠናከር እና የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ በማቋቋም ዙሪያ ከክልሎች ጋር ሰፊ የምክክር መድረኮች ማድረጉን አውስተው፤ ለሥራው አጋር ድርጅቶች ድጋፍ እንዲሰጡ የበርካታ ሀገራት ተወካዮችን የማነጋገር ሥራዎችም ሲሠሩ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ፣ አውሮፓ ኅብረት፣ አሜሪካ እና አውሮፓ ኅብረት ውስጥ ያሉ ሀገራትን በስፋት ኮሚሽኑ ማነጋገሩንና በቀጣይ አብረው ለመሥራት ፍላጎታቸው ገልፀዋል።

ኢፕድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *