ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከተለያዩ አገራት ትምህርት ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከዓለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ አገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጋር የፓናል ውይይት አካሂደዋል።
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ ላይ እያደረገች ያለውን ለውጥ እና ስራ አብራርተዋል።
በአጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ማንሳታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአፍሪካ ሚኒስትሮች ውይይትም የተካሄደ ሲሆን ዓለም አቀፋ የትምህርት ጉባኤ በብሪታኒያ እየተካሄደ ይገኛል።
ዋልታ
