Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

310 ግራም የወርቅ ማዕድን በመኖሪያ ቤታቸው ያከማቹ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ


310 ግራም የወርቅ ማዕድን በመኖሪያ ቤታቸው ያከማቹ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

በጋንቤላ ክልል አኟክ ዞን በዲማ ከተማ 310 ግራም የወርቅ ማዕድን፣ አንድ ኪ.ግ የወርቅ ቅላጭ መሰል፣ ከመቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ብር በላይ፣ አራት ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ከ101 መሰል ጥይቶች ጋር፣ ሶስት ሽጉጥ ከ14 መሰል ጥይቶች ጋር ይዘው የተገኙ 7 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር መዋል የቻሉት የማዕድን ግብይት አዋጅ ቁጥር 1144/2011 የተደነገገውን ክልከላ በመተላለፍ በሕገ-ወጥ መንገድ የወርቅ ማዕድን በመኖሪያ ቤታቸው በማስቀመጥ ለግል ጥቅማቸው ለማዋል ሲሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከህብረተሰቡ ባገኙት መረጃ መሰረት በመኖሪያ ቤታቸው ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረጉት ፍተሻ መሆኑ ታውቋል።

በተጨማሪም የፀጥታ አካላቱ በተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ቤት ባደረጉት ፍተሻ አራት ክላሽንኮቭ ከ101 መሰል ጥይቶች ጋር እና ሶስት የተለያዩ ሽጉጦች እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያን በመጣስ በግለሰብ ደረጃ ከመቶ ሺህ ብር በላይ በቤታቸው ውስጥ ከመቶ ሰላሣ አምስት ሺህ ብር በላይ አስቀምጠው በመገኘታቸው በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።

በመሆኑም በመሰል የወንጀል ድርጊቶች የተሰማሩ ግለሰቦችና ቡድኖችን በማጋለጥ አሳልፎ ለፀጥታ አካላት በመስጠት ኅብረተሰቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ኢዜኣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *