Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ለአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ የአቀባበልና የሽልማት መርኃ ግብር ተካሄደ

በአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ላይ ለተካፈለው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የአቀባበል እና የሽልማት መርኃ ግብር ተካሄደ፡፡

ለ5 ተከታታይ ቀናት በዛምቢያ – ኒዶላ ከተማ ሲካሄድ በቆየው የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የተካፈለው ቡድኑ በድምሩ 23 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ 4ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

በውድድሩ የወርቅ ሜዳሊያ ላሸነፉ ስድስት አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ30ሺሕ ብር ሽልማት እንዲሁም የብር ሜዳሊያ ላስገኙ 20 ሺሕ ብር እና ነሀስ ሜዳሊያ ላስገኙ አትሌቶች የ12 ሺሕ ብር ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የባህልና ስፓርት ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ስለተገኘው ውጤት ቡድኑን አመስግነው በቀጣይ ለሚኖረው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናና የኦሎምፒክ ውድድር ከወዲሁ መዘጋጀት እንዳለበት ፌዴሬሽኑን በማሳሰብ መንግሥት አትሌቲክስ ስፖርትን ለመደገፍ እና አብሮ በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

በመርኃ ግብሩ ላይ የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *