Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ፖል ካጋሜ በመከላከያ እና በደኅንነት ባለሥልጣናት ላይ ድንገተኛ ለውጥ ማድረጋቸው ተሰማ

የሩዋንዳ ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ የመከላከያ እና የደኅንነት ሚኒስትሮችና አዛዦች ለውጥ ማድረጋቸው ተሰማ::

ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜ በለወጧቸው ባለሥልጣናት ምትክ ÷ ጆቪኔል ማሪዛሙንዳን በመከላከያ ሚኒስትርነት ፣ ሌተናል ጄነራል ሙባራክ ሙጋንጋን ደግሞ በመከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦርነት ሾመዋቸዋል::

በተጨማሪም የሀገሪቱ የምድር ኃይል ዋና አዛዥ እና የመከላከያ ሠራዊቱ የመረጃና ደኅንነት በአዲስ አዛዥና ኃላፊ መተካታቸው ተሰምቷል፡፡

ሞዛምቢክን ለማገዝ በተሰማራው የሩዋንዳ ኃይል ላይም የአዛዦች ለውጥ ተደርጓል ነው የተባለው::

የሩዋንዳው ዘ ኒው ታይምስ እንደዘገበው ፥ ፕሬዚደንት ካጋሜ ባለፈው ሰኞ ምሽት ይፋ ያደረጉት ሹም-ሽር ያልተጠበቀና ድንገተኛ ነበር::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *