Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን የጥቁር ባህር የእህል ሥምምነትን ማራዘም በሚቻልበት አግባብ ላይ ከፑቲን ጋር ሊነጋገሩ ነው

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶኻን ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር የጥቁር ባህር የእህል ሥምምነትን ማራዘም በሚቻልበት አግባብ ላይ ሊነጋገሩ መሆኑን አስታወቁ።

ፕሬዚዳንቱ ከፑቲን ጋር ውሉን ማራዘምና ማደስ በሚቻልባት አግባብ ላይ በስልክ ለመነጋገር ማቀዳቸውን አር ቲ ዘግቧል።

ሩሲያ በጥቁር ባህር በኩል የዩክሬን የጥራጥሬ ምርቶች ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ የተደረሰው ሥምምነት ‘አፈጻጸሙ ጉድለት አለበት’ በሚል ዳግም እንደማታድስ አስታውቃለች።

ሥምምነቱ ባለፈው አመት ሐምሌ ወር ላይ የተመድ፣ ሩሲያ፣ ዩክሬን እና የቱርክ ተወካዮች በተገኙበት ነበር የተደረሰው።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም በተለያየ ጊዜ ሲራዘም ቆይቶ ሩሲያ ትናንት ገደቡ የሚያልቀውን ሥምምነት ማቋረጧን እና እንደማታድስ ይፋ አድርጋለች።

ለዚህ ደግሞ ሞስኮ የምግብና የማዳበሪያ ምርቶቿን ለገበያ እንዳታቀርብ የሚያደርገውን የምዕራባውያንን ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ ማንሳት አልቻለም በሚል ተመድን ወቅሳለች።

ይህ እስካልተተገበረ ድረስም ሩሲያ ለዚህ ሥምምነት ተገዥ እንደማትሆን የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትም ተመድ እና ቱርክ ሞስኮ ውሉን ለማራዘም ፍላጎት እንደሌላት መረዳታቸውን አረጋግጧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *