Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ግንቦት 30 የራያ እና ሰኔ 30 የምእራብ ትግራይ አስተዳደርን ለትግራይ ማስረከብ የተቆረጠ ቀጠሮ ነው

በምእራብ ትግራይ እና በራያ የትግራይ ህገመንግስታዊ መሬቶች ላይ የመቆመሪያ ግዜው እያበቃ ነው❗️


በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራ ላይ ውጥረቱ እየጨመረ በመምጣቱ፤ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በመጪዎቹ ቀናት አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡ በዚህ ጉብኝታቸው ከፌዴራል መንግስት፤ ከአፍሪካ ህብረት እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ስለስምምነቱ አፈጻጸም ሂደት ይወያያሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ትላንት በሰጠው መግለጫ “ከኢትዮጵያ እና ከትግራይ ጊዚያዊ መስተዳድር ባለስልጣናት ጋር በፕሪቶሪያ ስምምነትን አፈፃፀም ላይ አስቸጋሪ ጉዳዮችን በፖለቲካዊ ውይይት ለመፍታት እና ወደ ግጭት መመለስን ለማስወገድ” በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ለኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲላክ ተደርጓል በማለት አሳውቃለች።

በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ላይ ተሳታፊ የነበሩት የአፍሪካ ህብረት፤ አሜሪካ፤ አውሮፓ ህብረት እና የተበበሩት መንግስታት ስምምነቱ እንዲተገበር ሁሉንም እርምጃ ይወስዳሉ! ከትግራይ ላይ በወረራ የተያዙት ቦታዎች እንዲለቀቁ የአለም መንግስታት፤ የአፍሪካ ህብረት፤ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ቁርጠኛ አቋም እና ፍላጎት አላቸው፡፡

በአንጻሩ የብልጽግና መንግስት በመሃል ቁማር ለማጫወት ይፈልጋል፡፡ የአማራ ክልል ደግሞ ተቆጣጠጥሮ ለመቆየት እየጣረ ነው፡፡ በመሆኑም አዲስ ጦርነት እንዳያስከትል እና ትግራይን እንደገና ወደ ጦርነት ሊያስገባ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። ስለሆነም ሊፈጠር የሚችለውን ግጭቱን ለማስወገድ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት እንዲተገበር አሜሪካ ጫና ለመፍጠር አምባሳደሯን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ትልካለች፡፡

ስለዚህ የብልጽግና መንግስት በምእራብ ትግራይ እና በራያ ላይ የትግራይ እና የአማራ ህዝቦችን በማባላት እድሜውን ለማርዘም የሚያደርገው ቁማር ግዜው አብቅቷል፡፡ የትግራይ ፖለቲከኞች እና ህዝብ እንዲሁም አለማቀፉ ማህበረሰብ፤ ለብልጽግና መንግስት ሴራ እና ቁማር ምንም አይነት ቦታ የላቸውም፡፡ ግንቦት 30 የራያ እና ሰኔ 30 የምእራብ ትግራይ አስተዳደርን ለትግራይ ማስረከብ የተቆረጠ ቀጠሮ ነው ‼️
,,,d

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *