አቶ ጌታቸው አሰፋን በተመለከተ
“ጌታቸው አሰፋ ሲአይኤ (Stubbornly patriotic and ardent nationalist ብሎ ይጠራዋል (USA, CIA Doc. 7429)። የማይነቃነቅ አርበኛና ጠንካራ ሃገራዊነት ስሜት ያለው ማለት ነው። ሲኣይኤ የተለመደ ስልት አለቻቸው። መጀመርያ ደልለው ሊገዙህ ይጥራሉ። እምቢ ካልክ የሆነ ቁልፍ መረጃ ይዘዉብህ ወይ ታዘዘን አልያም እናጋልጥሃለን ብለው ብላክ መይል ለማድረግ ይሞክራሉ። ብላክ መይል ለማድረግ ካልቻሉ ሶስተኛው ማስገደል ነው። ጌታቸው አሰፋ ላይ ሁሉንም ሞክረዉታል። አልቻሉም። ሴራዉን ቀድሞ ስለደረሰው አንድ በአንድ አከሸፈባቸው።
አሁን ኢትዮጵያን በቀኝ አገዛዛችን ስር ናት የሚል እምነት ያደረባቸው አሜሪካዎች ጌታቸዉን የሚነካ ሪሶሊሽን እንዲወጣላቸው እየጠየቁ ይገኛሉ። የኛዎቹ ባንዳዎችም ፈንጥዘዋል። የተሰነዘረው ሃሳብ ነፃ ያልሆኑ እንደነ ጊኒ ወይም ቻድ አይነት ደካማ ህዝቦች ላይ የሚሰነዘር ክስ ነው። ጌታቸው አሜሪካ እንዳይሄድ፣ በስሙ ያለው ንብረት እንዲታገድ ምናምን የሚል ነው። ሲጀመር ጌታቸው ሙስናን የሚጠየፍ ቅኝ ግዛትን የሚጠላ ስለሆነ እነሱ ይፈፀምልን ያሉት ነገር ቢሆንም እንኳ በሂወቱ ምንም ተፅእኖ የሚያሳድር አይደለም።
አሜሪካዎች ዛሬ ግልፅ መልእክት አስተላልፈዋል፣ We Are The Real Bosses In Town እያሉን ነው። “በዉስጣዊ ጉዳያቹህ ገብቼ ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ያልከሰሰው ሰው ቢሆንም እኔ የናንተ ፖሊስና ፍርድ ቤት ነን” ብለዉናል። ከዚህ በላይ ዉርዴት የለም። ጌታቸው አሰፋ በቀዉስና በሽብርተኝነት በታመሰ ቀጠና አስተማማኝ ሰላም ማስፈን የቻለ Elite የደህንነት ሰው ነው። ድህረ ጌታቸው ኢትዮጵያ አይደለም አልሸባብን ልታኮላሽ ከድሬዳዋ ወደ ሀረር የሚሄደዉን የዉሃ ቱቦ ከሰፈር ጎረምሳ ማስጣል የማትችል ልፍስፍስ ሃገር ሆናለች። የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካ ቀኝ ግዛት ዉስጥ ያለ መንግስት አለመሆኑ የሚያስመሰክርበት አጋጣሚ ነው። ጌታቸው ግን አታግሎ ለድል ያበቃዉን ህዝብ ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሌት ተቀን ስራዉን እየሰራ ይገኛል።
በነሱ ግምገማ (USA, CIA Doc. 7429) “Getachew Assefa is, professionally incredible born man of profound intelligence, the invincible and the invisible creature.” ይሉታል:: “በሙያው አስገራሚ ለስራው የተፈጠረ ጀግና የማይሸነፍና የማይታየዉ ፍጥረት” ይሉታል። አሁን ዋናው ቁም ነገር ቀኝ ተገዝተናል ወይስ ሉዓላዊ ሃገር ነን? የሚል ከመንግስት ግልፅ እና አስቸኳይ መልስ የሚፈልግ ጥያቄ ነው።”
