Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ጅቡቲ ወደብ የደረሰው ከ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ ነው – ግብርና ሚኒስቴር

ጅቡቲ ወደብ የደረሰው ከ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀ በ2015/16 ምርት ዘመን የሚውል 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኮንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሞ ወደ ሀገር ውስጥ የማጓጓዝ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

እስከ ሰኔ 10/2015 ዓ.ም ድረስ ከ7 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ እየተጓጓዘ ነው ብሏል፡፡

የማጓጓዝ ስራው በመኪና እና በባቡር በፍጥነት እየተከናወነ ሲሆን አዳማ ካለው ባቡሩ ጣቢያ እንደደረሰ ወደ ኦሮሚያ፣ አማራና የሲዳማ ክልሎች ሲጓጓዝ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በክልሎች ያሉ የተለያዩ የህብረት ስራ ማህበራት የማጓጓዝ ስራውን በትኩረት እየሰሩ መሆኑንም ከግብር ሚኒስቴር ማህበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በቀጣይም ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶና አርብቶ አደሩ ለማቅረብ ሚኒስቴር በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *