እንዲፈቱም ለምክር ቤቱ ሥልጣን የሚሰጥ እንደሆነም ተገልጿል።
የዘንድሮው ጉባዔ በዋነኝነትም በሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን ጦርነቶችና ሶማሊያ ላይ መክሯል።
ዋና ጸሐፊው ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በጉባዔው መክፈቻ ላይ የሱዳንን ቀውስ አስመልክተው ተናግረዋል።
ዋና ጸሐፊው በሱዳን የተከሰተው ጦርነት አስከፊ ስቃይን አስከትሏል ያሉ ሲሆን “በመቶዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ቆስዋል እንዲሁም ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ተፈናቅለዋል” ብለዋል።
በሱዳን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስም ተፋላሚ ወገኖችን “ለሰላም ውይይትም ዕድል ስጡት” ሲሉ ጠይቀዋል።
bbc
