Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
ዜና ትግርኛ
0

ይህ ያስፈልጋል ተብሎ የቀረበው የገንዘብ መጠን በአገር ደረጃ ከኤክስፖርትና ከሌሎች ምንጮች ከሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ውጭ ያለውን ክፍተት ለመሙላት እንደሚውል ተናግረዋል፡፡

ይህንን ገንዘብ ለማግኘት ወሳኝ የሆነ ድርድር በቅርቡ እንደሚጀመር የገለጹት አቶ ተክለ ወልድ፣ የመጨረሻ ወሳኔ ላይ የሚደረሰውም ድርድሩ በሚያስገኘው ውጤት መሠረት ይሆናልም ብለዋል፡፡ ገንዘቡን ለማግኘት ኢትዮጵያ ከተቋማቱ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ለማስተናገድ በሚያስችል ደረጃ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ድርድር እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

 ከሚፈለገው ከ12 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ምን ያህል ሊገኝ እንደሚችል የተጠየቁት አቶ ተክለ ወልድ፣ ‹‹በእኛ ፕሮጀክሽን በእነሱና በእኛ መካከል የነበረው ክፍተት አሁን በጣም ጠቧል፡፡ ነገር ግን ገንዘቡ ብቻ ሳይሆን ከገንዘብ ጋር የሚመጡ መሥፈርቶች ስላሉ በዚህ ላይ ተከራክሮ መስማማት ያስፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡

በተለይም ከውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ላይ ሪፎርሙ ተግባራዊ በሚሆንበት የጊዜ ገደብ ላይ ከፍተኛ ክርክር ሊኖር እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ድርድሩ እንደሚፈለገው ከሄደ የአውሮፓውያኑ ዓመት ከማለቁ በፊት ብድሩ ሊገኝ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡  

አሁን ያለው ሁኔታ ተስፋ ያለው ነው የሚባለውም ድርድሩ ከቆመበት እንዲቀጥል በር በመከፈቱና የገንዘብ ተቋማቱ የኢትዮጵያን ጥያቄ ለመመለስ ቀና ሆነው መገኘታቸው መሆኑን ያመለከቱት አቶ ተክለ ወልድ፣ በተለይ የአሜሪካ ኮንግረስ የተጣሉትን ገደቦች ካነሳ በሌሎች የመደራደሪያ ጉዳዮች ላይ ከሁለቱም ወገን ግማሽ መንገድ ድረስ ሄደው ጉዳዩን እንዲሳካ ማድረግ የሚችሉበት ዕድል መኖሩን አክለዋል፡፡

ድርድሩ ቀላል ባይሆንም እነሱ ገንዘበ ለመልቀቅ የሚጠይቋቸውን መሥፈርቶች በጥንቃቄ ዓይቶ ውሳኔ መስጠትን የሚጠይቅም መሆኑን፣ ነገር ግን እነሱ የጠየቁት ጥግ ድረስ መንግሥት እንደማይሄድ አቶ ተክለ ወልድ አስታውቀዋል፡፡

ለምሳሌ የውጭ ምንዛሪ ፖሊሲው በምን ዓይነት መንገድ ሊስተካከል እንደሚችልም በዚሁ ድርድር የሚወሰን ስለመሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ይሰጣል የተባለው ገንዘብ ሳይለቀቅ መቅረቱን ያስታወሱት አቶ ተክለ ወልድ፣ አሁን ስምምነት ላይ ከተደረሰ ከቀድሞ የተሻለ ገንዘብ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *