Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የፌደራል ተቋማትን ለማስተሳሰር በ798 ሺህ ዶላር የተገነቡ የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ተመረቁ


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በወርልድ ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በ5 የፌደራል ተቋማት ያስገነባቸውን የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር፣ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ መታወቂያ ጽ/ቤት፣ ኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን እንዲሁም ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ለሚያስተሳስሩት 5 ስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች ግንባታ 798 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጪ መደረጉ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ የመንግሥት የስራ ስዓትን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲሁም ጊዜና ጉልበትን ለመቆጠብ የሚያስችል መሆኑን መሆኑን በትስስሩ ተጠቃሚ የሆኑት ተቋማት ተወካዮች ገልፀዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በዚሁ ወቅት፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ተግባራዊነት በአይሲቲና መሰል ዘርፎች ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፎች የተከፈለ መሆኑን እና በቀጣዩ ምዕራፍ በፌደራል ተቋማት፣ በክልሎች እና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች በአጠቃላይ በ20 ተቋማት መሰል የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍሎች የሚገነቡ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ኢዜኣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *