Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የፋይናንስ ጉዳዮች፤ የኢኮኖሚ ዕቅድና ውህደት ላይ ያተኮረው ጉባኤ በናይሮቢ ኬንያ እየተካሄደ ይገኛል


6ኛው የፋይናንስ ጉዳዮች፤ የኢኮኖሚ ዕቅድና ውህደት ላይ ያተኮረው የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጉባኤ በናይሮቢ ኬንያ እየተካሄደ ይገኛል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በሚኒስትሮች ደረጃ እየተደረገ ባለው ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ሚኒስቴር ዴኤታዋ አፍሪካ ከችግሮች ባሻገር በኢንቨስትመንት፥ ዘላቂ ዕድገትና የጋራ ብልጽግናን ማስፈን በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት የተሳተፉ ሲሆን የተለያዩ ሃሳቦችን አንስተዋል።

የአፍሪካ ሃገራት በህገወጥ መልኩ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪንና ፋይናንስን ከመከላከል አኳያ ጠንካራ ስርዓት መገንባትና ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ማስወገድ እንደሚገባ፣ ዘላቂ ልማትንና ኢንቨስትመንትን ከማሳደግ አኳያ የአፍሪካ መንግስታት በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት፤ የግሉ ሴክተርና የመንግስት አጋርነትን በማጠናከር የመሰረተ ልማት አውታሮችን መዘርጋት አስፈላጊነቱን አጽንዖት ሰጥተው አብራርተዋል።

በጉባኤዉ የአፍሪካ አካታች ዕድገትና ዘላቂ ልማትን በሚወስኑ (Drivers of Africa’s inclusive growth and sustainable development) ሁኔታዎች ዙሪያ ላይ መወያየት፤ የአፍሪካ ክልላዊ ውህደት የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም በቀጣይ የአፍሪካ ሃገራት ለውህደቱ የራሳቸውን የማይተካ ሚና እንዲጫወቱ በማድረግ ላይ ምክክር እየተደረገበት ይገኛል።
በፓናሉ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዉባቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *