የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ በግብጽ ሻርም አል-ሼይክ በተጀመረው የአፍሪካ ልማት ባንክ የአመራሮች ቦርድ ዓመታዊ ስብስባ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ሚኒስትሩ እየተካፈሉበት ያለው ስብስባ የግሉ ዘርፍ ፋይናንስ ለአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት በሚቻልባቸው አማራጮች ላይ እንደሚያተኩር ተመልክቷል።
በተለይም የግሉ ዘርፍ ለአህጉሪቱ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከልና ዘላቂ ልማት እያደረገ ባለው አስተዋፅኦ ላይ ስብሰባው እንደሚመክርበትም የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
