የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ምሽቱን ተመልሰዋል።
ኦላፍ ሾልስ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት ዛሬ ሲሆን ፤ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በታላቁ ቤተመንግስት ውይይት አድርገዋል።
ምሽቱን ጉብኝታቸው አጠናቀዉ ሲሄዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አሸኛኘት እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ፡ ኢዜኣ
