የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች በበጀት ዓመቱ ባለፍት ዘጠኝ ወራት ከ 2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቋል ።
ከነዋሪውና ከንግዱ ማህበረሰብ ገቢው መሰብሰቡ ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እድገት መሳካት ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሀመድ ተናግረዋል።
ሰራተኞችና አመራሮች ተቀናጅተው መስራታቸው ለተገኘው ስኬታማ የገቢ አሰባሰብ አስተዋጽኦ ማድረጉን የድሬዳዋ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘገባ አመልክቷል ።
ኢዜኣ
