የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በሂሮሺማ የሚካሄደው የቡድን 7 አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጃፓን ገብተዋል።
እንደ ሬውተርስ ዘገባ ፕሬዚዳንቱ በስብሰባው ላይ መሳተፋቸው፣ ለበለጸጉት የዓለም ሀገሮች የተለመደውን የድጋፍ ተማፅኖ ለማቅረብ ዕድል ይሰጠቸዋል።
ዜሌንስኪ በዓለም የመጀመሪያዋ የኒውክሌር ጥቃት ሰለባ በሆነችው የጃፓኗ ሂሮሺማ ከተማ ላይ መገኘታቸው፣ ምዕራቡ ዓለም በሞስኮ ላይ ለሚያነሳው የኒውክሌር አረር የመጠቀም አዝማሚያ ክስ ትኩረት እንዲሰጠው ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የቡድን 7 አባል ሀገራት የሆኑት አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን እና ካናዳ፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ፈጽማዋለች በሚሉት ወረራ፣ በቻይና እና ታይዋን መካከል ባለው ውዝግብ እንዲሁም ዓለም በኢኮኖሚ ደኅንነት ላይ የገጠማትን ግዙፍ ፈተና በተመለከተ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሰሞኑ በዓረብ ሊግ ሰብሰባ ላይ ተገኝተው “እንደ አለመታደል ሆኖ፣ በዓለም ውስጥ እና እዚህ፣ ከእናንተ መካከል ጦርነቱን እና ሕገ-ወጥ እስራትን እንዳላየ የሚያልፉ አንዳንድ ሀገራት አሉ” ማለታቸውን ተከትሎ ከዓረቡ ዓለም ሚዲያ እና ምሁራን ትችት ሲቀርብባቸው መሰንበቱን የዘገበው ደግሞ ሩሲያ ቱደይ ነው።
ትግቲቪ
