Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከፊታችን ሐምሌ 3 ቀን ጀምሮ ይሰጣል

የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

በ2014 ዓ.ም የሕግ መውጫ ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ ያላስመዘገቡ ተማሪዎችም በዚሁ ጊዜ ፈተናውን የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተናን ለመሥጠት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ፋና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *