የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሄዷል፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ላለፉት 12 ወራት በልዩ ልዩ መርሐ-ግብሮች ሲያከናውን ቆይቷል።
መጠቃለያውን በማሰመልከት በትላንትናው ዕለት በፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የቁንጅና ፋሽን ውድድር፣ በአስተዳደር ሠራተኞች እና መምህራን መካከል የእግር ኳስ ጨዋታ ተከናውኗል፡፡
በዛሬው ዕለትም “ለጥበብ እሮጣለሁ” በሚል መሪ ቃል ሕዝባዊ ሩጫ ተካሂዷል።
በበዓሉ ላይ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋስው፣ የባሕር ዳር ከተማ ከንቲባ ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር)፣ የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ አመራሮች እና ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር) በበዓሉ ላይ የአሁኑ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ በ1955 ዓ.ም የተቋቋመው የባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በ1965 ዓ.ም የተቋቋመው የባሕር ዳር መምህራን ኮሌጅ ተዋህደው በ1992 ዓ.ም መመሥረቱን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት በዘጠኝ ግቢዎች 15 አካዳሚዎች፣ 5 ኮሌጆች፣ 4 ኢንስቲትዩቶች፣ 2 የትምህርት ፋኩልቲዎች፣ 2 የአካዳሚክስ ትምህርት ቤቶች አሉት ብለዋል የዩንቨርሲቲው ፕሬዚዳንት።
ዩኒቨርሲቲው 75 ከመቶ በላይ የድህረ-ምረቃ መርሐ-ግብሮች ላይ አተኩሮ እየሠራ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ስፔሻሊቲ እና ሰብ ስፔሻሊቲ መርሐ-ግብሮችን ጨምሮ 437 የትምህርት ፕሮግራሞች እንዳሉት ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው በነዚህ ሁሉ መርሐ-ግብሮቹ የኅብረተሰቡን ኑሮ የሚያሻሽሉ ሥራዎችን ቀድሚያ ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“በተለይም ትልቅ ሀብታችን የሆነው ዓባይ ለሀራችን ዘላቂ ጥቅሞችን በሚሰጥበት መልኩ በምርምር የታገዘ ሥራ ይሠራል” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህ በዚህ መርሐ-ግብር ላይ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ አገልግሎትን ማዕከል አድርጎ እየሠራ መሆኑን ተናግረው በዚህም 200 ሺህ የሚሆኑ ሙያተኞችን ለሀራችን እና ለዓለም አበርክቷል ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው 60ኛው ዓመቱን ሲያከብር የ60 ዓመታት የስኬት እና ፈተና ጉዞውን መገምገሙ ከራሱ ልምድ ሰፊ ትምህርት እንዲያገኝ ረድቶታል ብለዋል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች ሀገርን ሊያዘምኑ የሚችሉ እና ለኅበረተሰቡ ተደራሽ የሚሆኑ ሥራዎችን እንደሚሠራም እምነታቸው መሆኑን አደም ፋራህ መናገራቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው።
የዩኒቨርሲቲው የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

ዋልታ