Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ


የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ ከአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያዩ።

ሚኒስትር ዴኤታው “በውይይታችን ዋና ፀሀፊውም ሆኑ ተመድ ለኢትዮጵያ እያደረጉት ላለው ድጋፍ ያለንን አድናቆት ገልጬላቸዋለሁ” ብለዋል።

በድህረ ጦርነት ወቅት የሚከናወኑ የመልሶ ግንባታ ስራዎች በማገዙም ረገድ በኢትዮጵያ እና በተመድ መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ከስምምነት መደረሱንም ነው ያመለከቱት።

አምባሳደር ምስጋኑ፣ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ስለሚገኝበት ደረጃም ገለፃ አድርገውላቸዋል።

አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ የሰሜኑን ግጭት ፈታ በፍጥነት ለውጥ እያሳየች በመሆኑ መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣናው ቁልፍ ሚና የምትጫወት ሀገር እንደመሆኗም፥ በሀገሪቱ ያለው ሰላምና መረጋጋት ለአካባቢው አወንታዊ ትርጉም አለው ብለዋል።

የተገኘውን ሰላም ለማፅናት ሀገሪቱ የምታደርውን ጥረት ተመድ እንደሚደግፍ ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ምንጪ፡ ኢዜኣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *