Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ለ42ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች አስመረቀ

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ለ42ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ42ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች በደማቅ ወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች፣ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

ተመራቂዎቹ ኢትዮጵያ የሚል ስያሜ የተሰጣቸውና ከመከላከያ ሠራዊቱ፣ ከባህር ሃይልና ከፌዴራል ፖሊስ የተውጣጡና ለረጅም ወራት የሰለጠኑ የኮማንዶ አባላት መሆናቸው ተገልጿል።

በዝግጅቱ ላይ ተመራቂዎች የተለያዩ ወታደራዊ ትዕይንት ያሳዩ ሲሆን÷ በዕለቱ የክብር እንግዳና በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ንግግር ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *