Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የከተማ አስተዳደሩ እስከ ሰኔ 30 ተከራይን ማስወጣትም ሆነ ኪራይ መጨመር እንደማይቻል አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ከቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል አስታወቀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በተደረገ ክትትል ደርሰንበታል ብሏል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑን ይታወሳል::

በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት አይቻልም ማለቱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *