Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
ዜና ትግርኛ
0

የኦሮሞ ፈሰቲቫል

የኦሮሞ ምሁራን የፓለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ስምምነትና ውሳኔዎች

ሲያትል ፣ ዋሽንግተን
ሐምሌ 31 ቀን 2025 (እ.ኤ.አ.)

የኦሮሞ ምሁራን የፓለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ቀን ውይይት በሲያትል ዋሽንግተን ሐምሌ 31 ቀን 2025 ተካሂዷል።በኦሮሚያ፣ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይትና ትንተና ካደረግን በኋላ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ ተስማምተን ውሳኔዎች ላይ ደርሰናል።

አንደኛ፡ አሁን በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የኦሮሞን ህዝብ ከዚህ በፊት ታይቶ ለማይታወቅ ሰቆቃ እና ጭቆና እንዳጋለጠው ተገንዝበን ይህ አገዛዝ መወገድ እንዳለበት ተስማምተናል። ይህ ቡድን ፀረ ኦሮሞ ተግባራትንና ፖሊሲዎችን እየፈፀመ በዚህ ብሄር ውስጥ ለመደበቅ የሚያደርገውን ሙከራ አጥብቀን እናወግዛለን። በተመሳሳይ አንዳንድ ወገኖች በዚህ ቡድን ‘የኦሮሞ መንግሥት’ ብለው የሚጠሩት የተሳሳተ አካሄድ ከነባራዊው እውነታ የራቀና ተቀባይነት የሌለው ከንቱ ጥረት ነው።

ሁለተኛ ፡ የአብይ አህመድ ጨቋኝ አገዛዝ በሁሉም የሀገሪቱ ብሄረሰቦች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት አጥብቀን እናወግዛለን።

ሶስተኛ ፡ የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶችን (ኦነግ-ኦነሠ: ኦፌኮ እና ኦነግ) በተደራጀ መንገድ አስፈላጊውን ለውጥ በማምጣት መጪውን ሽግግር ስኬታማ ለማድረግ በሚየደርጉት እንቅስቃሴዎች በሁሉም ዘርፍ ለመተባበር ተስማምተናል።

አራተኛ፡ የአብይ አህመድ መንግስት የስልጣን መሰረት አድርጎ ከተጠቀመባቸው ስልቶች አንዱ በብሄረሰቦች መካከል ግጭት መፍጠር ነው። በኦሮሞ ህዝብና ወንድማማች ብሄሮች መካከል ጥርጣሬና ግጭት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን በመረዳት ሁሉም የሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦችና ዜጎች ይህንን እኩይ አገዛዝ ለመለወጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወቅታዊ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አምስተኛ፡ የአብይን ብልፅግና መንግስት የሚያገለግሉ ወታደራዊና የፖለቲካ ሃይሎች የአገዛዙን ሥልጣን ከመጠበቅ የህዝብን ጥቅም ወደ ማስከበር እንዲሸጋገሩ ጥሪ እናደርጋለን።

ስድስተኛ ፡ በኦሮሞ የፓለቲካ ኃይሎች መካከል የተጀመረው ውይይት እንዲቀጥልና ከሌሎች የአገሪቱ ብሄረሰቦችና ዜጎች ጋር ምክክር ለማድረግ ተስማምተናል።

ሰባተኛ፡ የአብይ አህመድ አገዛዝ እድሜውን ለማራዘም በህዝቦች መካከል ግጭት በመፍጠር መፈናቀልን ሲፈጥር መቆየቱን እንረዳለን። ህዝቡም ይህንን ስልት አውቆ በመካከላቸው ያለውን አንድነትና ወንድማማችነት እንዲጠብቅ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በመጨረሻም የተጀመሩት ውይይቶችን የሚያካሂድና የተደረጉትን ውሳኔዎችን ለማሳካት አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራ እንዲጀምር ተደርጓል።

አንድነታችን በነፃነት ይፀናል፣
ድል በትግላችን ይመጣል!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *