Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የኦሮሚያ ክልል የግብርና ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ስብሰባ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት እየተካሄደ ነው

የኦሮሚያ ክልል የግብርና ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት 2ኛ ዙር ስብሰባዉን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በክልሉ እየተተገበሩ ያሉ ኢኒሼቲቮችን የእቅድ አፈጻጸም በመገምገም አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክር ተገልጿል።

በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ እና የፌዴራል የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የክልሉን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ዕዉን ለማድረግ በክልሉ እየተተገበሩ የሚገኙ የተለያዩ የግብርና ኢኒሼቲቮችን ከ15 ወደ 28 ለማሳደግ አቅዶ እየሠራ መሆኑን በመድረኩ ተጠቅሷል።

የክልሉ መንግስት የግብርና ትራንስፎርሜሽን ዕውን ለማድረግ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማትና በሌሎች ኢኒሼቲቮች የእርሻ ትራክተሮችን፣ ኮምባይነሮችን፣ የዉሃ ፖምፖችን፣ ምርጥ ዘሮችን፣ የተለያዩ የግብርና ግብአቶችን በማቅረብ እና የገበያ ትስስርን በመፍጠር የክልሉን አርብቶ አደሮችን በመደገፍ ላይ አንደሚገኝም ተጠቁሟል።

የበጋ መስኖ ስንዴ፣ የቢራ ገብስ፣ የወተት ሃብት ልማት፣ የንብ እርባታ፣ የሙዝ፣ የአቮካዶ፣ የቡና፣ የሩዝ እና የቡናና ሻይ ልማቶች በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች በክላስተር እየተተገበሩ ካሉ ኢኒሼቲቮች መካከል ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን መገለፁን ኦቢኤን ዘግቧል። የኦሮሚያ ክልል የግብርና ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት በይፋ ተቋቁሞ ስራ የጀመረዉ ባለፈዉ አመት ሲሆን ምክር ቤቱ በ7 ክላስተሮች የተመሠረተ ነዉ።

ምንጭ፡ኢዜኣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *