Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
ዜና ትግርኛ
0

የኦሮሚያ ክልል የልማት ድርጅቶች በተጠናቀቀዉ የበጀት አመት 5 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ትርፍ ማግኘታቸዉ ተገለጸ



የክልሉ የልማት ድርጅቶች ገበያን ከመፍጠርና ተወዳዳሪ ከመሆን አልፈዉ ትርፋማና ዉጤታማ እንዲሆኑ በትጋት ሊሰሩ እንደሚገባ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ ገለፁ።

የልማት ድርጅቶች የ2015 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2016 ዓ.ም የማጠቃለያ ዕቅድ ተገምግመዋል። በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማው ላይ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አደሬ አሰፋ፣ በተጠናቀቀዉ የበጀት አመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የክልሉ የልማት ድርጅቶች ዕዉቅና እንሠጣለን ብለዋል።

የልማት ድርጅቶች በተጠናቀቀዉ የበጀት 5 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ትርፍ ማግኘታቸዉ በስራ አፈጻጸም ሪፖርቱ ተጠቅሷል።

የልማት ድርጅቶቹ የአራት አመታት አጠቃላይ ገቢም በ64.5 ከመቶ ዕድገት እያሳየ መምጣቱ ተገልጿል። በቀጣዩ የበጀት አመትም 60 ቢሊዮን ብር ገቢ በማሰባሰብ 8 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ለማግኘት ታቅዷል።

በግምገማዉ ላይ የተገኙ አቶ አወሉ አብዲ የክልሉ የልማት ድርጅቶች ገበያን ከመፍጠርና ተወዳዳሪ ከመሆን አልፈዉ ትርፋማና ዉጤታማ እንዲሆኑ በትጋት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። የልማት ድርጅቶቹ በኮንስትራክሽን፣ በአግሮ ፕሮሰሲን፣ በኢንዱስትሪና ማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በደንና እርሻ ልማት፣ በፋይናንስ፣ በንግድ፣ በአገልግሎትና በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ተሰማርተዉ በመስራት ላይ የሚገኙ ናቸዉ።

በኮንስትራክሽንና መሠል የልማት ስራዎች ላይ የተሠማሩ አንዳንድ ድርጅቶች ትርፋማ: በግንባታ: ወደ ምርትና አገልግሎት ስራ በመግባት ላይ የሚገኙ ሲሆኑ ትፋማ መሆን ያልቻሉና የመክሰር አደጋ ያጋጠማቸዉ ጥቂት ካምፖኒዎችም አሉ።

በግምገማዉ ላይ የተገኙ የልማት ድርጅቶቹ ኃላፊዎች የተሰጣቸዉን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የዉጭ ምንዛሬ እጥረት: የግብአት አቅርቦት: የመሠረተ ልማት ዝርጋታና የጸጥታ ችግር ተግዳሮት እንደፈጠረባቸዉ ተሳታፊዎቹ አንስተዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አወሉ አብዲ የልማት ድርጅቶቹን ትርፋማና ዉጤታማ ለማድረግ ተገቢዉን ድጋፍ እናደርጋለን: በልማት ድርጅቶቹ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘዉ ሪፎርምም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ተቋማቱ የክልሉን የልማት እንቅስቃሴ ከመደገፍ: ገበያንና የስራ ዕድል ከመፍጠር: ገበያን ከማረጋጋትና ሃብት ከመፍጠር ረገድ ትልቅ ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል።

ኢፕድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *