የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቤተ መንግስት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ተካሄደ።
በቤተ መንግስቱ የግንባታ ማስጀመር ስነ ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ እና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
የፕሮጀክቱ ጠቅላላ ግንባታ በ 6.5 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚያርፍ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
የፕሮጀክቱ ዲዛይን የገዳ ስርዓት ለዘመናት እያበረከተ ያለውን ጠቀሜታ የሚገልጽ ነው ተብሏል።
በ2 ዓመታት ጊዜ ይጠናቀቃል የተባለውን የፕሮጀክት ግንባታ የሚያከናውነው የቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው።
ኢቢሲ
