Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የኦሮሚያ ሴቶች ፌዴሬሽን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው


የኦሮሚያ ሴቶች ፌዴሬሽን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን “የሴቶች ጥምረት ለሁለንተናዊ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል በአዳማ ከተማ ገልመ አባገዳ እየተካሄደ ይገኛል።

ጉባኤው ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በቆይታውም የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና ሥራ አስፈፃሚዎች ይመረጣሉ፣ የኦዲት እና ቁጥጥር ኮሚቴ የ7 ዓመት የሥራ ክንውን ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል፤ የ3 ዓመት የሥራ አቅጣጫ ይሰጣል ተብሎም ይጠበቃል።

የኦሮሚያ ሴቶች ፌዴሬሽን እንዲጠናከር የሚናቸውን ለተወጡ ተቋማት የምስጋና ምስክር ወረቀት ይሰጣል።

በጉባኤው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ሎሚ በዶን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ኢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *