የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፋርማስቲካል ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ኢንቨስት ከሚያደርጉ 5 የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈራረሟል።
በስምምነት ፊርማው ላይ የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ፤ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ዘርፍ መሰማራታቸው የኢትዮጵያን የጤና ሽፋን ከማሳደጉ በተጨማሪ በዘርፉ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት በኩልም ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል።
ኩባንያዎቹ ወደ ሥራ ሲገቡ መድኃኒት እና የሕክምና ግብአቶች በማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚያቀርቡ ሲሆን ከ1 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድልን እንደሚፈጥሩ ተገልጿል።
ኮርፖሬሽኑ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ከ8.2 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንት ካስመዘገቡ 10 የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር የስምምነት ፊርማ መፈራረሙም ይታወሳል።
እነዚህ ኩባንያዎች ወደ ሥራ ሲገቡ ከ7 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ ዕድልን እንደሚፈጥሩ ተገልጿል።
ኢንቨስትመንቶቹን የሚያስተናግደው የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ በሙሉ በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሠራ የተቋቋመ እጅግ ዘመናዊ የኢንቨስመንት ማዕከል መሆኑን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፡ ኢዚኣ
