የኢትዮጵያ እና የደቡብ አፍሪካ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ስሰባው ረጅም አመት ያስቆጠረውን የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዉ ግንኙነት ያጠናክራል ብለዋል።
“ኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ በነበረችበት ወቅት የአፍሪካን ችግር በአፍሪካውያን በሚለው መርህ ደቡብ አፍሪካ ችግራችንን በስምምነት እንድንፈታ ትልቅ እገዛና አስተዋጽኦ አድርጋችኋል። ይህም የሁሉን አገራት ጠንካራ ግንኙነት ያመለክታል” ብለዋል አቶ ደመቀ።
የሁለቱን አገራት ትብብርና ግንኙነት ለማጠናከር የጋራ የሚኒስትሮች ስብሰባ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ያሉት አቶ ደመቀ፣ በተለያዩ ዘርፎች የመግባቢያ ስምምነቶች እንደሚፈጸሙም ገልጸዋል።
በስብሰባው ከሁለትዮሽ ውይይት ባለፈ በአህጉራዊና በአለም አቀፍ ግንኙነት ዙሪያዎች ውይይቶች በማድረግ ለችግሮች መፍትሄ ማፈላለግ ያስፈልጋልም ብለዋል።
