Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የኢትዮ- የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮችን ማስተዋወቅ አላማው ያደረገው የኢትዮ- የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቢዝነስ ፎረም በአቡ ዳቢ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በፎረሙ የኢንቨስትመት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ለባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች እና ለዘርፉ ምቹነት የተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን እና ኮሚሽነር ለሊሴ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ዝግጁነት አስረድተዋል፡፡

ፎረሙ የኢንቨስትመንት ከባቢውን በማነቃቃት እና ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የኢንቨትመንት ግንኙነት በማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው መግለፃቸውን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፋና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *