Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የኢትዮጵያ ከተሞች የውኃ አገልግሎቶች ፎረም እየተካሄደ ነው

ሰኔ 13/2015 (ዋልታ) 14ተኛው ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ ከተሞች የውኃ አገልግሎቶች ፎረም በድሬዳዋ እየተካሄደ ይገኛል።

ፎረሙ በከተሞች የንጹህ መጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ጉዳዮች እና በዘላቂ መፍትሄዎች ላይ በመምከር አቅጣጫዎች የሚያስቀምጥ መሆኑም ተመላክቷል።

በውይይቱ ላይ በከተሞች የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግርን በተሻለ እና በተደራጀ መንገድ ለመፍታት የተከናወኑ ተግባራት በተሞክሮ ይቀርባል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ከተሞች የውኃ አገልግሎት ፎረም ፀሐፊ ቡሽራ መሐመድ ከመድረኩ የሚገኙ የተሻሉ ተሞክሮዎች ወደ ሌሎች የአገሪቱ ከተሞች ለማስፋት ፎረሙ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

አገር አቀፍ የኢትዮጵያ ከተሞች የውኃ አገልግሎቶች ፎረም በከተሞች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ላይ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የራሱን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

ፎረሙ በድሬዳዋ ከተማ በዘርፉ የተሠሩ ስራዎችን እንደሚጎበኙም ገልጸዋል።

በፎረሙ ላይ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እና የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል እና የክልሎች የዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *