የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑክ ከቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ የሥራ ሀላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡
ልዑኩ በሁለቱ ሀገራት መካከል በፈረንጆቹ 2022 በተፈረመው እና የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት እና ንግድ አማራጮችን በጋራ ማስተዋወቅን አላማ ባደረገው የመግባቢያ ሰነድ አፈፃፀም ሂደት ላይ መክሯል፡፡
በዚሁ ወቅት ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን እና የቻይና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጀኔራል ሊ ያንግ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
በቻይና ቤጂንግ ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑክ ከቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ የሥራ ሀላፊዎች ጋር መምከሩን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
FBC
