Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
ዜና ትግርኛ
0

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በግብጽ አዲስ እየተገነባ ያለውን የካይሮ ከተማን ጎበኙ


ከተለያዩ ከተሞች እና ተቋማት የተወጣጣው የልዑካን ቡድን የካይሮ ከተማን የሕዝብ ብዛት መጨናነቅ ለማስተንፈስ መልሶ የማልማትና ለወደፊቱ ትውልድ የሚሆን ዘመናዊ፣ ሁለገብና ምቹ ከተማን ለመገንባት የተሠሩ ሥራዎችን ጎብኝቷል።

ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት፤ ገጠርን ከከተማ አስማምቶ ለማደግ የተከናወኑ ተግባራትንም ተመልክቷል።

በጉብኝቱ ወቅት ከካይሮ ከተማ አስተዳደር ጋር ከተሞችን በማዘመን፣ ወቅቱን የዋጀ የከተማ የመሠረተ ልማት ግንባታንና የተጨናነቁ የከተማ አካባቢዎችን ስለማስተካከል በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

ኢትዮጵያና ግብጽ በባህል፣ በታሪክና በሕዝብ ብዛት ተቀራራቢነት ያላቸው በመሆኑ የልዑካን ቡድኑ ያገኘው ልምድ በየከተሞቹ ሊተገበሩ የሚችሉ መሆናቸውን አባላቱ ገልጸዋል።

ጉብኝቱ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በግብጽ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተከናወነ ነው።

በጉብኝቱ የፌደራል አመራሮች፣ የአዲስ አበባ፣ የአዳማ፣ የባሕር ዳርና የሐዋሳ ከንቲባዎችም ተሳትፈዋል።

ኢፕድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *