በአፍሪካ ለ33ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአፍሪካ ህጻናት ቀን አስመልክቶ ማጠቃለያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የአፍሪካ የህጻናት ቀን እ.ኤ.አ ሰኔ 16 የሚከበር ሲሆን በዚህ ዓመት “ሰላም፣ ፍቅር ፣ እንክብካቤ እና ጥበቃ ለሁሉም ህጻናት” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
ባለፉት ጊዜያት የአፍሪካ ህጻናት በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት አድሎ ይደርስባቸው እንደነበርና አሁን ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የአህጉሪቱን ህጻናት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰሩ እንደሚገኙ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ህጻናት በቴክኖሎጂ ራሳቸውን በማብቃት ዘመኑ የሚፈልገውን የቴክኖሎጂ ስርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑና ራሳቸውን እንዲያበቁ እየተሰራ ነው ተብሏል።
ማጠቃሊያ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባባር የተዘጋጀ ሲሆን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ::
ዋልታ
