የአዲስ አበባ ጅቡቲ ኮሪደር አዲስ በጸደቀው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ኮሪደር ፕሮጀክት መሠረት በ730 ሚሊየን ዶላር ወጪ የግንባታ ማሻሻያ ሊደረግለት መሆኑን የዓለም ባንክ አስታውቋል፡፡
ባንኩ ባወጣው መረጃ ፕሮጀክቱ ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከርና በኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ አቅምን ለማጎልበት ያለመ ነው። ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ኮሪደር ፕሮጀክት ቀጣናዊ ውህደትንና አካታች ዕድገትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝም ተገልጿል።
ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ኮሪደር ፕሮጀክቱ ከሚኤሶ-ድሬዳዋ ያለውን መንገድ ለማዘመንና ለማስፋፋት ይውላል። ይህም የኢትዮጵያን የሎጂስቲክስ ብቃት በማሻሻል የሀገሪቱን የንግድ ተወዳዳሪነት እንደሚያሳድገው የዓለም ባንክ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።
በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከዋናው መንገድ ጋር በማገናኘት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንደመሚያሳድግም ባንኩ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።
ኢ ፕ ድ
