ዛሬ የመንግስት የፀጥታ አካላት በአንዋር መስጊድ ሰጋጆች ላይ ተኩስ የከፈተው የተቃውሞ ድምፅ ስለ ተሰማ አይደለም።
ተኩሱ የተሰማው የተቃውሞ ድምፅ በመሰማቱ አይደለም።
ተኩስ መከፈት ሲጀምር አንድም የተቃውሞ ድምፅ አልነበረም። ሶላት ተሰግዶ ልክ እንዳበቃ ሸህ ጡሀ ዱአ ማድረግ ሲጀምሩ ነው የጥይት እሩምታ በሰጋጆች ላይ መውረድ የጀመረው።
ምንም ያላደረገን ህዝብ ተቃውሞ እንኳ ሳያሰማ ገና ሶላት ሰግዶ ዱኣ እያደረገ ሳለ ነው የጥይት እሩምታ የወረደበት።
የአንዋር መስጊድ ይህ ያልተለመደ ጭካኔን በአደጋ ጊዜ አዛን በማድረግ ህዝበ ሙስሊሙን በመጥራት አድኑን ብሏል።
የቆሰሉትን የሚያነሳ አካል የለም። መዳን ሲችሉ የሞቱ አሉ። አንቡላን በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
ሰጋጆች እንዳይወጡ ዘሪያውን ከቦ ነው በጥይት የደበደባቸው። ዙሪያውን አፍኖ አዋከባቸው።
በርካቶች በቀጥታ በሚተኮስ ጥይት ተመተዋል። የሟች ቁጥር እንዳይጨምር ያስፈራል።
ይሄ ሁሉ ግፍ ለምን!?
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄን በደል ይወቅ ! ይሄን ግፍ ይስማ!
መረጃቲቪ
