Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ ተጠናቀቀ


ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ ባለዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

በኮንፈረንሱ የለውጡን ስኬቶች በማፅናት እና አሁናዊ ችግሮችንም ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በፅናት እና በአንድነት መቆም እንደሚገባ ስምምነት ላይ መድረስ መቻሉ ተገልጿል።

በክልሉ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች በጥልቀት እንደተገመገሙም ተጠቅሷል።

በአቋም መግለጫው እንደተጠቀሰው፣ በለውጡ የፖለቲካ ምኅዳር ማስፋት፣ ግንባታቸው የተቋረጡ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ፣ የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎች በሕጋዊ መንገድ ምላሽ የሚያገኙበትን ዕድል መፍጠር የለውጡ ማሳያዎች ናቸው።

የክልሉ መንግሥት ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት ሁሉንም ዋጋ እየከፈለ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

ኢዜኣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *