Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
ዜና ትግርኛ
0

የአለም ባንክ ፕሬዘዳንት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጎበኙ


የአለም ባንክ ፕሬዘዳንት ሚስተር አጃይ ባንጋ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጎበኙ፡፡

በስፍራው ሲደርሱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ፐሬዝዳንቱ በጉብኝታቸው በአገሪቱ እየመነጨ ያለው ኢነርጂ ለሀገር ውስጥ እንዴት እንደሚተላለፍ፣ እንደሚከፋፈል ፣ እንደሚሰራጭ ፣ አገልግሎቱን ከማዳረስ አኳያ እየተሰራ ያለውና ከጎረቤት ሀገራት ጋርም ያለውን ትስስር አስመልክቶ እንዲሁም በአለም ባንክ ድጋፍ የተሰሩና እየተሰሩ ስላሉ የሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች ፣ በባንኩ በኩል እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችና በቀጣይ እቅድ ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል፡፡

ፕሬዘዳንት አጃይ ባንጋ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው አጠቃላይ ገለጻ በማመስገን፤ የኤሌክትሪክ ሀይል ለአንድ ሀገር እድገት የሚጫወተው ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡

በእለቱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው እና ሌሎች እንግዶችም መገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *