Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ብቁ ዜጋን ለማፍራት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል – ትምህርት ሚኒስቴር


የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ብቁ ዜጋን ለማፍራት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የቅድመ አንደኛ ደረጃ የትምህርት ጥራት እና የ4ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የምዘና ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በጥናቱ ከ50 በመቶ በላይ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ከ8ኛ ክፍል 12 በመቶ እንዲሁም ከ4ኛ ክፍል 20 በመቶ ብቻ መሆናቸው ተመላክቷል።

ለትምህርት ጥራት ጉድለት ደግሞ እንደችግር የተለዩ ጉዳዮች የስርዓተ ትምህርት መሳሪያዎች እጥረት፣ የመምህራን እጥረት ወይም የመምህራን ተነሳሽነት ማጣት በትምህርት ቤቶች ለልጆች ምቹ የሆኑ መሰረተ ልማት አለመኖር የሚሉት ከብዙ ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው።

በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራትን በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚመጣ ባለመሆኑ ትውልድ ላይ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ።

ኢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *