የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በእንግሊዝ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ትምህርት ሚኒስትሩ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከብሪታኒያ የልማትና የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አንድሪው ሚቼል እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የልጃገረዶች ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ከሆኑት ሄለን ግራንት ጋር በትምህርት ዘርፍ ትብብርን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።
በውይይታቸውም ሚኒስትሩ በትምህርቱ ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የማሻሻያ ስራዎችን በተለይ ለትምህርት ጥራት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደሆነ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ሄለን ግራንት በበኩላቸው የሴቶች ትምህርት ሊሻሻል በሚችልበት ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
የዘንድሮው የትምህርት ጉባኤ “አዲስ ጅማሮ፣ የመማር ባህልን ማሳደግ፣ የመቋቋም አቅምን መገንባት፣ ዘላቂነትን ማሳደግ፤ በንድፍ ሃሳብ የተደገፈ ጠንካራና የተሻለ ትምህርት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ እንደሚገኝ እና የሁሉም ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች እየተሳተፉ መሆናቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ዋልታ
