የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመገኘት የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ የፈተና አሠጣጥ ሂደቱን ተመልክተዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከሚኒስትር ደኤታው ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ሲቪል ሠርቪስ ዩኒቨርሲቲ እና በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ኢንስቲቲዩት ምልከታ አድርገዋል።
በምልከታቸውም ሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና በጥሩ ሁኔታ እየተሠጠ መሆኑን ለመገንዘብ መቻሉን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ዛሬ የተጀመረው የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና እስከ ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም ለተከታታይ አራት ቀናት ይሰጣል።
የመጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ሚስጥራዊነቱና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
