በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 50 በመቶ በላይ ውጤት ያስመዘገበ ተመራጭ ባለመኖሩ ምርጫው በድጋሚ ሊካሄድ ነው።
እየተቆጠረ ባለው የቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ያለፉትን 20 ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶጋን ብርቱ ፉክክር ገጥሟቸዋል።
በምርጫው ለማሸነፍ በ50 መቶ በላይ ማስመዝገብ ግዴታ ሲሆን እስካሁን በተካሄደው ቆጠራ 49.42 በማስመዝገብ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን እየመሩ ሲሆን ተከታያቸው ከማል ክሊቻሮግሉ 44.95 እየተከተሉ ይገኛሉ።
የቆጠራ ሂደቱ 99 በመቶ እንደተጠናቀቀም ቲ አር ቲ ወርልድ እና አናዶሉ እየዘገቡ ይገኛል።
ሁለቱም ተፎካካሪዎች ሀገር ለመምራት የሚያስችል 50 በመቶ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ባለመቻላቸው ድጋሚ ምርጫ ግንቦት 20 ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
ከምርጫው አስቀድሞ ሁለቱም ተፎካካሪዎች ምርጫውን በእርግጠኝነት እንደሚያሸንፉ የተናገሩ ሲሆን በድጋሚ ምርጫው ብልጫ እንደሚወስዱ ተፎካካሪው ከማል ክሊቻሮግሉ እየገለጹ ይገኛሉ።
ኢዜኣ
