የተፈጠረው የነዳጅ እረጥት …
“ነገ፣ መጋቢት 25 ቀን 2016ዓ.ም ይቀረፋል” – የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
ከሰሞኑ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ከወትሮው በተለየ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎችና የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ጅቡቲ ላይ የዘነበውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ድልድይ በመሰበሩ ነው ብሏል።
በተጨማሪም ነዳጅ የጫነ አንድ የነዳጅ ቦቴ ተገልብጦ መንገድ መዘጋጋት በማስከተሉ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ይስማ አለም ምህረቱ ለኢቲቪ አስረድተዋል፡፡
ችግሩን ለመቅረፍ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በድሬደዋ በኩል እንዲገቡ ተደርጓል ያሉት ስራ አስፈጻሚው ይሄንኑ ተከትሎ ትናንት መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰአት ጀምሮ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መግባት መጀመራቸውን አረጋግጠዋል፡፡
አክለውም ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም እና ነገ ነዳጅ የጫኑ ተጨማሪ ቦቴዎች እንደሚገቡ እና ችግሩ እስከ ነገ ጠዋት ድረስ እንደሚቀረፍ ገልጸዋል፡፡
@gettu
