Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

የተጀመረው የፍትህ ተቋማት የለውጥ ፍኖታ ካርታ ትግበራ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ

ፍትህ ለሰላም፣ ለዘላቂ ልማትና ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ ሚና ስላለው የተጀመረው የፍትህ ተቋማት የለውጥ ፍኖታ ካርታ ትግበራ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።

3ኛው ሀገር አቀፍ የህግ አውጪዎች የጋራ ምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

አፈ ጉባኤ ታገሰ መድረኩ በመንግስታት መካከል ያለውን ግንኙነት ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1231/2013 መሰረት በማድረግ በፌዴራል እና በክልሎች መካከል ያለውን ግንኙነትን ለማጠናከር በየስድስት ወሩ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል።

ፍትህ ለማረጋገጥና ለማጠናከር በፌዴራል የፍትህ ተቋማት የተጀመረው የፍትህ የለውጥ ፍኖታ ካርታ በየደረጃው ያሉ የፍትህ ተቋማት ለመተግበር መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።

“ፍትህ ለሰላም፣ ለዘላቂ ልማት፣ ለፖለቲካና ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ ሚና አለው” ሲሉም አፈ ጉባኤው ተናግረዋል።

በህግ አውጪዎች መካከል የሚደረገው ውይይት ዘላቂ ሰላምን በማስፈን፣ ዋስትና ያለው ዲሞክራሲ ለማረጋገጥ እና ፈጣን እድገት በማስመዝገብ አንድ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያግዛልም ብለዋል።

የክልሎች እና የብሄረሰቦች ምክር ቤቶች እየተሳተፉበት በሚገኘው የምክክር መድረክ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ከማጠናከር ባሻገር መልካም ተሞክሮዎች የሚለዋወጡበት እንደሆነም ጠቁመዋል።

መድረኩ በፌዴራል ደረጃ በፍትህ ሥርዓቱ ላይ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በክልሎችም ለማጠናከር የሚያግዝ ምክክር ይካሄድበታል ተብሏል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ እውነተኛ የዴሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት በየደረጃው የሚገኙ የፍትህ ተቋማት ተቋማዊ ነፃነታቸው ተጠብቆ በሰው ኃይል እና በቴክኖሎጂ ታግዘው መስራት ይጠበቅባቸዋል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *