Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

“የተቋሙን ደህንነት በማረጋገጥ ረገድ የአየር ኃይል ጥበቃ ክፍለ ጦር ውጤታማ ተግባር እያከናወነ ነው” ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ


የተቋሙን ደህንነት በማረጋገጡ ረገድ የአየር ሃይል ጥበቃ ክፍለ ጦር ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ ነው ሲሉ የአየር ሃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ።

አዛዥ ይህን የተናገሩት በጥበቃ ክፍለ ጦር የሥራ ቦታ የተሰሩትን ቢሮዎች የመዝናኛ ቦታዎችን እና የልማት ስራዎችን ተዘዋዉረው ከጎበኙ በኋላ ነው።

የአየር ኃይል ጥበቃ ክፍለ ጦር የተቋሙን ደህንነት እና ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ ከዚህ በፊት እንደችግር ሲነሱ የነበሩ ክፍተቶችን በአጭር ጊዜ በአስተማማኝ ሁኔታ በማስወገድ የአየር ኃይልን የግዳጅ አፈፃፀም ውጤታማ ማድረግ መቻላቸውንም ገልፀዋል።

የጥበቃ ክፈለ ጦሩ አባላት በቢሾፍቱና አካባቢው ጭምር የህብረተሰቡን ሰላም በመጠበቅ ፅንፈኞችን በመታገል አኩሪ ተግባር ፈፅመዋል።

ከግዳጅ ጎን ለጎን በራስ ተነሳሽነት የሥራ ቦታቸውን እና አካባቢያቸውን በማልማት ያደረጉት ጥረት ለሌሎችም የተቋሙ ክፍሎች ምሳሌ መሆኑን ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ተናግረዋል።

የአየር ኃይል ጥበቃ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ወንዱ ወልዱ በበኩላቸው የጥበቃ ክፈለ ጦሩ ለሚሰጠው ማንኛውም ተልዕኮ የተለየ ትኩርት በመስጠት ግዳጁን በሚገባ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ኮሎኔል ወንዱ የአየር ኃይል አዛዥ እና ከፍተኛ አመራሮች ያደርጉት ልዩ ክትትልና ድጋፍ የጎላ አስተዋፅኦ እንደነበረው ጠቁመው የአየር ሃይል አዛዥ የሠጡት አሥተያዬት የሥራ ተነሳሽነትን እና ሞራልን የሚገነባ ነው ማለታቸውን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓም

ኢፕድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *